1. የእህቶች አገልግሎት ዘርፍ ተግባርና ኃላፊነት
- ከኮሚቴ አባላት ጋር በመሆን እቅድ ማዘጋጀት፣ እንዲጸድቅ ለመሪዎች ጉባኤ ማቅረብና ሲጸድቅ በእቅዱ መሰረት እንዲካሄዱ ማድረግ፣
- በአጥቢያይቱ የሚገኙ እህቶች እንደ እግዚአብሔር ቃል መንፈሳዊ ህይወታቸው የታነጸ እንዲሆን ትኩረት ሰጥቶ ማገልገል፣
- ከትዳር ጓደኛቸው፣ ከልጆቻቸው፣ ከቤት ሰራተኛና ከጎረቤት ጋር የሚኖራቸው ግንኙነት በጎ ምስክርነት ያለው እንዲሆን ጌታን የሚያሳይ እንዲሆን ከጾታ በተያያዘ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የምናያቸው እናቶች ምስክርነትና ፈለግ የተከተለ እንዲሆን መምከር፣ ማስተማርና መከታተል፣
- ከጾታ በተያያዘ የሚከሰቱ ማህበራዊ ችግሮች ለመፍታት እህቶች እንደ እግዚአብሔር ቃል ጥሩ መንፈሳዊ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ጥረት ማድረግ፣
- የሴቶች ክርስትያናዊ ህብረት የተጠናከረ እንዲሆን በውጭ ላሉም ሴቶች ትምህርት ሰጪ እንዲሆን ወንጌልን ለሌሎች በማድረስ ረገድም ተሳትፎዋቸው ካለው እያደገ እንዲሄድ አሃዛ ለውጥና እድገት ለማምጣት ጥረት ማድረግ፣
- በሳምንታዊ ፕሮግራሞች የሚሳተፉ እህቶች ቁጥር አሁን ካለው የሚያድግበትን ስልት በመንደፍ ውጤት ለማሳየት መስራት