1. የዝማሬና አምልኮ አገልግሎት ዘርፍ ተግባርና ኃላፊነት
- በዝማሬ አገልጋዮች ላይ መዝሙርና አምልኮን በግልና በጋራ በመለማመድ በቃሉ ላይ የተመሰረተ የህይወት ለውጥ እንዲያመጡ ማድረግ፣
- የአምልኮ ፕሮግራሞች ወንጌል ተኮር እንዲሆን ማድረግና ጥራት ማሳደግ፣
- የዘርፉን አባላት ቁጥር ማሳደግ፣
- በበዓላትና ልዩ ዝግጅቶች ኮንፍራንሶች ሲኖር የጋራ አገልግሎቶች እንዲኖሩ ማድረግ፣
- በአጥቢያ በህብረቶችና በጸሎት ቤቶች የሚኖረው አገልግሎት በእቅዱ መሰረት እንዲሳካ ማድረግ፣
- ከዝማሬና አምልኮ አገልግሎቶች የተያያዙ አልባሳት የሙዚቃና የድምጽ መሳሪያዎች እንዲሟሉ ክትትል ማድረግ፣
- ከሌላ አጥቢያ የአገልግሎት ጥሪ ሲመጣ መደበኛው አገልግሎት ሳይጓደል የሚሸፈንበትን ሁኔታ ማመቻቸት፡፡
- ነባርና አዳዲስ አገልጋዮችን በቅርብ በመከታተል በእግዚአብሔር ቃል በጸሎት፣ በዝማሬ እውቀቶች ኮትኩቶ ማሳደግ፣
- የመዘምራንን ህይወትና የአገልግሎት ትጋት በመከታተል መምከርና ማበረታታት፣
- እንደ አስፈላጊነቱ ሌሎች የመዘምራን ቡድኖችን ማደራጀት፣
- ለአገልግሎቱ አመቺ የሆኑ ሥልጠናና ትምህርት እንዲያገኙ አግባብ ካላቸው ዘርፎች በመመካከር ማሳካት፣
- የጋራ የሆነ የጾምና ጸሎት ጊዜ እንዲኖራቸው ማድረግ፣
- ለመቀራረብና የመንፈስ አንድነትን ለመጠበቅ የሚያስችሉ የአንድነት ፕሮግራሞችን ማዘጋጀት፡፡