1.1. የህብረቶችና ጸሎት ቤቶች ማደራጃ ዘርፍ ተግባርና ኃላፊነት
- በከተማና በገጠር የሚገኙ ጸሎት ቤቶችን ህብረቶችን በተመለከተ ዓመታዊ እቅድ ያወጣል፡፡ በመሪዎች ጉባኤ ያጸድቃል፡፡
- ፕሮግራሞችን በእቅዱ መሰረት መካሄዳቸውን ይከታልል፡፡
- ከአስተባባሪዎች ጋር በመመካከር ጸሎት ቤቶች ወደ ህብረት፣ ህብረቶች ወደ አጥቢያ እንዲያድጉ፣ አዳዲስ ጸሎት ቤቶች እንዲመሰረቱ ለማድረግ የሚስችሉ ጥናቶች በማድረግ ለመሪዎች ጉባኤ ሂሳብ ያቀርባል፡፡
- ስለህብረቶችና ጸሎት ቤቶች ከህብረቶችና ኮሚቴዎች ጋር በመሰባሰብ ወቅታዊ የእቅድ አፈጻጸም ግምገማ በማድረግ ጠንካራ ጎኖች የበለጠ እንዲጠናከሩ ደካማ ጎኖች እንዲሻሻሉና እንዲስተካከሉ ያደርጋል፡፡
- ወንጌል በገባበት ሁሉ ጠንካራ ጸሎት ቤትና ህብረት እንዲመሰረት ያላሰለሰ ዳሰሳ በማድረግ ሃሳብ ያቀርባል፡፡ ለተግባራዊ እንቅስቃሴ የሚያመቹ ሁኔታዎችን ያመቻቻል፡፡
1.2. የከተማ /የገጠር ህብረት/ ጸሎት ቤት ተግባርና ኃላፊነት
- የዓመታዊ ዕቅድ ረቂቅ በማዘጋጀት ከዘርፉ ጋር ተመካክሮ እንዲጸድቅለት ያቀርባል፡፡
- የከተማ ህብረቶች/ጸሎት ቤቶች አስራት፣ መባ፣ ስጦታ በኩራትና ሌሎች ገቢዎች በወቅቱ ተሰብስበው ወደ አጥቢያ ቤተክርስቲያን እንዲገቡ ያደርጋል፡፡
- የገጠር ህብረቶች/ጸሎት ቤቶች አስራት መባ፣ ስጦታ በኩራትና ሌሎች ገቢዎች በወቅቱ ተሰብስበው በሥራ ላይ እንዲውሉ በማድረግ ለአጥቢያ ቤተክርስቲያን በመመሪያው መሰረት ሪፖርት ያደርጋል፡፡
- ከኮሚቴ አባላት ጋር በመሆን በእቅዱ መሰረት ፕሮግራሞች እንዲካሄዱ ያደርጋል፡፡
- ህብረቱን ወደ አጥቢያ /ጸሎት ቤቱን ወደ ህብረት ለማሳደግ የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎች እንዲሟሉ የማደራጀት ስራዎችን ይሰራል፡፡
- የአገልግሎት ዘርፎችን ያደራጃል፡፡
- ከዘርፉ ጋር የህብረቱ/የጸሎት ቤቱ ችግሮች እንዲቀረፉ፣ ሌሎች ጸሎት ቤቶች በአካባቢው እንዲቋቋሙ ይሰራል፡፡
- ዘርፉ በሚጠራው ስብሰባ ይካፈላል፡፡
- ወቅታዊ ሪፖርት ለዘርፉ ያቀርባል፡፡