1.1. የጸሎት አገልግሎት ዘርፍ
- በቤተክርስቲያን አገልጋዮችና ምዕመናን በጸሎት እንዲበረቱ ያነሳሳል፣ የጸሎት ፕሮግራሞች ያዘጋጃል፣
- የጸሎት ቡድኖችን ያደራጃል፡፡
- መጽሐፍ ቅዱሳዊ የሆኑ ቋሚ የጸሎጽ ርዕሶችን ያዘጋጃል፡፡
- የጠቅላለ አገልጋዮች አዳር ጸሎት በፕሮግራሙ መሰረት እንዲካሄድ ያደርጋል፡፡
- የጠቅላላ አባላት ሳምንታዊ፣ ወራዊ እና ዓመታዊ የጾም ጸሎት ኮንፈረንስ እንዲካሄድ ያደርጋል፡፡
- ጸሎት ነክ ትምህርቶች አንዲሰጡ ያደርጋል፡፡
- ከአስተባባሪዎች የሚቀርቡ ሪፖርቶችን አጠናቅሮ ለመሪዎች ጉባኤ ያቀርባል፡፡
1.2. ወራዊ የጾም ጸሎት
- የተለያዩ ስልቶችን ነድፎ ተግባራዊ በማድረግ በዚህ ፕሮግራም የሚሳተፉ ምዕመናን ቁጥር እንዲጨምር ጥረት ያደርጋል፡፡
1.3. የረቡዕ ጾም ጸሎት
- የተለያዩ ስልቶችን ነድፎ ተግባራዊ በማድረግ በዚህ ፕሮግራም የሚሳተፉ ምዕመናን ቁጥር እንዲጨምር ጥረት፡፡
- አገልጋዮችን እንዲጋበዙና እንዲያገለግሉ ያደርጋል፡፡
1.4. የጥሞና ወቅታዊ ጸሎት
- የተለያዩ ስልቶችን ነድፎ ተግባራዊ በማድረግ በዚህ ፕሮግራም የሚሳተፉ ምዕመናን ቁጥር እንዲጨምር ጥረት ያደርጋል፡፡
- የሁሉንም ዘርፎች ፍላጎት ግምት ውስጥ በማስገባት ሁሉንም የሚያሳትፍ ፕሮግራም ያዘጋጃል፡፡
- ከተለያዩ አቅጣጫዎች የሚላኩ የጸሎት ርዕሶች እንዲጸለይባቸው ያስተባብራል፡፡
1.5. የአዳር ጸሎት
- የተለያዩ ስልቶችን ነድፎ ተግባራዊ በማድረግ የምዕመናን የአዳር ጸሎት ፍሬያማ እንዲሆን በፕሮግራም የሚሳተፉ ምዕመናን ቁጥር እንዲጨምር ጥረት ያደርጋል፡፡
- የአገልጋዮች የአዳር ጸሎት በዕቅድ እንዲመራ ፕሮግራሞችን ያዘጋጃል፡፡
1.6. የጸሎት ቡድኖች ማደራጀትና ማካሄድ
- በተጠኑ የጸሎት ርዕሶች ላይ የ24 ሰዓት ሰንሰላታማ የጸሎት ፕሮግራም በማዘጋጀት ያልተቋረጠ ጸሎት እንዲደረግ ጥረት ያደርጋል፡፡
- የተለያዩ ስልቶችን ነድፎ ተግባራዊ በማድረግ በዚህ ፕሮግራም የሚሳተፉ ምዕመናን ቁጥር እንዲጨምር ጥረት ያደርጋል፡፡