1. የወንጌል አገልግሎት ዘርፍ ተግባርና ኃላፊነት
- የወንጌል አገልግሎት ዘርፍ አጥቢያይቱ በሩቅ አካባቢ ወንጌል ወደ አልደረሰባቸው ቦታዎች ሚሽነሪዎችን ለመላክ አካባቢያዎችንና ተዛማጅ ሁኔታዎችን ጥናት ያደርጋል፣
- ለዚሁ አገልግሎት የሚያስፈልግ በጀት ያፈላልጋል፤ ምዕመናን ያስተባብራል፣
- እንደአስፈላጊነቱ ከሌሎች አጥቢያዎችና መንፈሳዊ ድርጅቶች ጋር በመተባበር አገልግሎቱ የሚካሄድበትና የሚጠናከርበትን ስልት ይቀይሳል፣
- ሚሽነሪ የመላክ አገልግሎት ከዓመት ወደ ዓመት እየሰፋ እንዲሄድ ይሰራል፡፡ የወንጌል ማበርተኞች ቁጥር እንዲጨምር ይሰራል፡፡
- ስለ አገልግሎቱ መረጃዎችን አደራጅቶ ይይዛል፤ ለወንጌል ማበርተኞች ወቅታ መግለጫ ያቀርባል፣
- ሚሽነሪዎች ትምህርትና ስልጠና እንዲያገኙ፣ የሚሽን ኮንፈረንስ እንዲካሄድ ያደርጋል፣
- በሚሽን አገልግሎት ወደ ጌታ የመጡ ወገኖች አምልኮ የሚያካሂዱበት ጸሎት ቤትና ህብረት ለማጠናከር ድጋፍ የሚያገኙበትን ስልት ይቀይሳል፣
- የወንጌል ምስክርነት እንዲካሄድ ስልት ይቀይሳል አስተባባሪዎች ጋር በመመካከር የወንጌል ምስክርነት በስፋትና በጥልቀት የሚካሄድበትን ያቅዳል፤ የስራ ክትትል ያደርጋል፡፡
- የምስክርነት ጓዶችን ያደራጃል፡፡
- በተወሰነ ጊዜ ከአስተባባሪዎች ጋር በመሰባሰብ የተከናወኑ ሥራዎች ይገመግማል፣
- በየወቅቱ የተጠናከረ ሪፖርት ለመሪዎች ጉባኤ ያቀርባል፡፡
1.1. የሩቅ ወንጌል ሚሽን
- ጸጋው ያላቸውን ሰዎች ለሩቅ ወንጌል አገልግሎት እንዲሄዱ ያነሳሳል ያበረታታል፡፡
- ወንጌል ወዳልሰሙ ጎሳዎች የወንጌል መልእክተኞችን አሰልጥኖ እንዲላክ ያደርጋል፡፡
- እምነትን ባህልንና የኑሮ ደረጃን መሰረት ያደረገ የወንጌል ስርጭት እንዲካሄድ ያደርጋል፡፡
- የሩቅ የወንጌል የአገልግሎት እንቅስቃሴ ጥናት በማድረግና በመከታተል እንዲጠናከር ጥረት ያደርጋል፡፡
- ወንጌል ወደ አልደረሰባቸው ቦታዎች ሚሽነሪዎች ለመላክ አካባቢዎችና ሁኔታዎች ከተጠኑ በኋላ አጋር ቤተክርስቲያኖች ጋር ለመስራት ያመቻቻል፡፡
- ዘርፉ በሚጠራው ስብሰባ ይካፈላል፡፡
- ወቅታዊ ሪፖርት ለዘርፉ ያቀርባል፡፡
1.2. የወንጌል ምስክርነት
- ወንጌል ወዳልሰሙ ሰዎች የወንጌል መስካሪዎችን አሰልጥኖ እንዲላኩ ያደርጋል፡፡
- እምነትን፣ ባህልንና የኑሮ ደረጃን መሰረት ያደረገ የወንጌል ስርጭት እንዲካሄድ ያደርጋል፡፡
- በተያዘው ዓመታዊ ዕቅድ መሰረት በገጠርና በከተማ ወንጌል እንዲመሰከር ከምስክርነት ጓድ ጋር በመሆን ይሰራል፡፡
- ከዘርፉ በመመካከር በተለያዩ አቅጣጫዎችን ዘዴዎች የወንጌል ምስክርነት ተጠናሮ እንዲካሄድ ስልት ይቀይሳል፡፡
- በምስክርነት የሚያገለግሉ ሰዎች ቁጥር እያደገ እንዲሄድ ስልት በመቀየስ ተጨባጭ አሃዛዊ ለውጥ ለማምጣት ተግቶ ይሰራል፡፡
- ዘርፉ በሚጠራው ስብሰባ ይካፈላል፤ ወቅታዊ ሪፖርት ያቀርባል፡፡