የሀዋሳ ሙሉ ወንጌል አማኞች አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን
HAWASSA FULL GOSPEL BELIEVERS’ LOCAL CHURCH
ራዕይ(ምሳ 29፡18)
ተልዕኮ(ማቴ 28፡19-20)
ዕሴቶች
|
Vision(Prov. 29 : 18 ) To see a healthy and strong church that ፡-
Mission(Matt.28:19-20) To make disciples by
Values
|
የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተ ክርስቲያን መሰረታዊ የክርስትና እምነት መግለጫ
- ስድሳ ስድስቱን የብሉይ እና የሐዲስ ኪዳን መፃሕፍት የያዘው መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር እስትንፋሳዊ ቃል ፣ ምንም ስህተት የማይገኝበት ፣ እምነትን እና ተግባርን በሚመለከት ሁሉ የመጨረሻው ሥልጣን ያለው ፣ ሕያው እና ዛሬም የሚሠራ ፣ እንደ ሆነ እናምናለን ፡፡
- እግዚአብሔር አብ ፣ በእግዚብሔር ወልድ እና በእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ፣ አንድ አምላክ ፣ እናምናለን ፡፡
- በመፍጠር ሥራ ፣ ፍጥረትን በመጠበቅ ፣ በመግለጥ ፣ በመዋጀት እና በመጨረሻው ፍርድ በእግዚአብሔር ፍጹም ስልጣን እና የበላይነት እናምናለን ፡፡
- ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከአብ የተላከ መሆኑን ፣ በመንፈስ ቅዱስ መፀነሱን ፣ ከድንግል ማርያም መወለዱን ፣ ፍጹም ሰው ፍጹም አምላክ መሆኑን ፣ ለሰው ልጆች ቤዛ ሆኖ በመስቀል ላይ መሞቱን ፣ መቀበሩን ፣ በሶስተኛው ቀን በአካል ከሙታን መነሳቱን ፣ ወደ አብ ማረጉን እና አሁንም በአብ ቀኝ ሆኖ ስለ እኛ እንደሚማልድ፣ ደግሞም በሕያዋን እና በሙታን ሊፈርድ በክብር እና በግርማ እንደሚመለስ እናምናለን ፡፡
- መንፈስ ቅዱስ የመለኮት ባሕሪያት ሁሉ ያሉት ፍጹም አምላክ እንደሆነ እና አምልኮ እና ስግደት እንደሚገባው እናምናለን ፡፡
- ሰው በእግዚአብሔር አምሳል መፈጠሩን ፣ በኃጢአት መውደቁን እና በዚህም ምክንያት የእግዚአብሔር ቁጣ እና ፍርድ ያለበት በደለኛ መሆኑን እናምናለን ፡፡
- ሰው ከኃጢአት ዕዳ ፣ ኃይል እና ቅጣት ፣ ሊድን የሚችለው ኃጢአት የሌለበት የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ የሰው ምትክ ሆኖ በፈጸመው የቤዛነት ሥራ ብቻ በመሆኑ ፣ ኃጢአተኛ በእግዚአብሔር ጸጋ በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን ብቻ እንደሚፀድቅ እናምናለን ፡፡
- ኃጢአተኛ በኃጢአቱ ተፀፅቶ ንሰሐ እንዲገባ ፣ በኢየሱስ ክርስቶስ አምኖ ዳግመኛ በመውለድ አዲስ ፍጥረት እንዲሆን መንፈስ ቅዱስ በሕይወቱ እንደሚሠራ እናምናለን ፡፡
- መንፈስ ቅዱስ በአማኝ ሕይወት ውስጥ እንደሚኖር ፣ አማኙ በመንፈስ ቅዱስ ሲጠመቅ ኃይል እንደሚቀበል እና በልሳን እንደሚናገር ፣ በየጊዜው በመንፈስ ቅዱስ እንደሚሞላ እናምናለን ፡፡
- መንፈስ ቅዱስ ዛሬም ቤተ ክርስቲያንን ለማነጽ ለአማኞች ልዩ ልዩ የፀጋ ስጦታዎችን በማካፈል ፣ ድውዮችን በመፈወስ ፣ አጋንንትን በማውጣት እና ተዓምራትን በማድረግ እንደሚሠራ እናምናለን፡፡
- ቤተ ክርስቲያን በክርስቶስ የተሰጣትን የታላቁን ተልዕኮ አደራ በመወጣት ወንጌልን ለሰዎች ሁሉ እንድትሰብክ እና አማኞችን ደቀ መዛሙርት በማድረግ ለክርስቶስ አካል መታነጽ አስፈላጊውን ሁሉ መፈፀም እንድትችል መንፈስ ቅዱስ ሐዋሪያትን፣ ነብያትን ፣ ወንጌል ሰባኪዎችን እረኞችን እና አስተማሪዎችን እንዲሁም ሌሎች የአገልግሎት ስጦታዎችን እንደሚሰጥ እናምናለን ፡፡
- ከእግዚአብሔር መንፈስ ዳግም የተወለዱ ሁሉ በሚገኙባት ፣ የክርስቶስ አካል በሆነች ፣ በአንዲት ቅድስት ቤተክርስቲያን እናምናለን ፡፡
- ጌታችን እና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ባዘዘው መሰረት ፣ ዳግም የተወለደ አማኝ ከክርስቶስ ሞት እና ትንሳኤ ጋር መተባበሩን ፣ እንዲሁም ለኃጢአት መሞቱን እና ለጽድቅ መነሣቱን ለመግለጽ በአብ ፣ በወልድ እና በመንፈስ ቅዱስ ስም በውኃ ውስጥ በመጥለቅ እንደሚጠመቅ ፣ እንዲሁም ጌታ ዳግም እስከሚመጣ ድረስ ሞቱን ለመናገር ፣ ከጌታ እና ከአማኞች ጋር ያለውን ህብረት መግለጽ ፣ የጌታን እራት እንደሚካፈል እናምናለን ፡፡
- በሙታን ትንሳኤ በኃጢአን ላይ በሚደርሰው የዘላለም ፍርድ ፣ አማኞች በሚቀበሉት የዘላለም ሕይወት እናምናለን ፡፡